• English

ማሳሰቢያ Ethiopia

ስዊድን፡ያለ፡የቤተሰብ፡አባል፡ጋር፡ሄዶ፡ለመኖር፡በሚመለከት፡ በስዊድን፡ኤምባሲ፡ለማመልከት፡ሲፈልጉ፡አስፈላጊውን፡አገልግሎት፡ከኤምባሲው፡ውጪ፡ካሉ፡ህገ-ወጥ፡ሰዎች፡ከማግኘት፡ይቆጠቡ።

አንዳንድ፡ግለስቦች፡በሀሰት፡የስዊድን፡የማይግሬሽን፡ጽ/ቤትን፡ወይንም፡በአንዳንድ፡ሀገሮች፡ያሉ፡የስዊድን፡ኤምባሲን፡እንወክላለን፡እንደሚሉ፡የስዊድን፡የውጪጉዳይ፡ሚኒስቴር፡መረጃ፡ደርሶታል።እነዚህ፡ግለስቦች፡የኤምባሲ፡መግቢያ፡ቀጠሮን፡ማሳጠር፡እንችላለን፡በማለት፡ገንዘብ፡ከባለጉዳዬችይጠይቃሉ።ስለሆነም፡ማንንኛውም፡አመልካች፡መገንብ፡ያለበት፡በየትኛውም፡ሀገር፡ያለ፡የስዊድን፡ኤምባሲ፡ሆነ፡የቆንስላጽ/ቤት፡እነዚህን፡ከመሰሉ፡ግለሰቦች  ወይንም፡እንሰጣለን፡ከሚሉት፡አገልግሎት፡ጋር፡ምንም፡ዓይነት፡ግንኙነት፡የለውም።ኤምባሲ፡ለመግባት፡የሚያስችል፡ማንኛውም፡ቀጠሮ(የቃለመጠይቅቀጠሮ)ወይንም፡ለቃለመጠይቅ፡ወደ፡ኤምባሲ፡ለመምጣት፡የሚያስችል፡ቀጠሮ፡ሁሉ፡የሚያዘው፡በእያንዳንዱ፡ኤምባሲ፡ሲሆን፡ቀጠሮ፡ለመስጠት፡ማንኛውም፡የስዊድን፡ኤምባሲ፡ክፍያ፡አይጠይቅም።በሌላ፡በኩል፡ስዊድን፡ያለየቤተሰብ፡አባል፡ጋር፡ለመኖር፡የሚሞላ፡ማመልከቻን፡የሚቀበለው፡የስዊድን፡ኤምባሲ፡ብቻ፡ነው።  የስዊድን፡መንግሥታዊ፡መ/ቤቶችን፡እንወክላለን፡በማለት፡በሀሰት፡የሚቀርቡ፡ግለሰቦች፡ካሉ(ካጋጠምዎ)፡ወይንም፡እንዳንድ፡አገልግሎት፡ለመስጠት፡ኤምባሲው፡ከሚጠይቀው፡የገንዘብ፡ መጠን፡በተጨማሪ፡ክፍያ፡በተለያዩ፡ግለሰቦች፡ከተጠየቁ፡በሚከተለው፡የኢሜል፡አድራሻ፡ኤምባሲውን፡ያሳውቁ። (ambassaden.addis-abeba@gov.se).

Last updated 12 Aug 2021, 9.59 AM